ጎሕ ቤቶች ባንክ አክሲዮን ማሕበር (በምሥረታ ላይ ያለ) የውክልና መፈጸሚያ ቅጽ (Representation Form)

ጎህ ቤቶች ባንክ አ/ማ በጥንቃቄ የምስረታ ጉባዔውን በውክልና  ለማካሄድ በዝግጅት ላይ  ነው!!

አሁን ባአጋጠመን ሁኔታ  በሺኅ የሚቆጠሩ ባለአክሲዮኖችን በአዳራሽ መሰብስብ አይቻልም :: ጉባዔውን በውክልና በጥቂት ባለአክሲዮኖች ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ በመሆኑ የባንኩ ባለአከሲዮኖች በጉበዔው  በውክልና እንድትሳተፉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

የውክልና ፎርሙን DOWNLOAD NOW የሚለውን በመጫን ያውረዱ፡፡ በጥንቃቄ ሞልተው በፎረሙ ላይ በተመለከተው ኢሜል ወይም በፖሰታ ቤት እስከ ሰኔ 15፣ 2012 ይላኩ፡፡

በአካል መምጣት አይመከርም፡፡ የግድ ከሆነ ኦሎምፒያ፣ ጌቱ ኮመርሺያል ፊት ለፊት በሚገኘው ባህር ህንጻ 8ተኛ ፎቅ ለዚህ ሲባል  ወደአዘጋጀነው ቢሮአችን  ይምጡ፡፡

በዚህ አጋጣሚ የአክሲዮን ሽያጭ እስከ ሰኔ 15፣ 2012  መራዘሙን በደስታ እንገልጻለን፡፡

አክሲዮኖቹን ከ50 000 ብር ጀምሮ መግዛትና ቢያንስ ግማሹን በመክፈል የባንኩ መሥራች  መሆን ይቻላል፡፡

አክሲዮኖቹ በተለያዩ ባንኮች እየተሸጡ ነው፡፡

ይህን አስቸጋሪ ወቅት በዘዴ፣ በትግስታና በእውቀት አሳልፈን ጎሕ ሲቀድድ ባንካችን አብቦ ያፈራል፡፡

በቅሎ ቤት ከቶታል ማደያ አጠገብ ኦሜዳድ ያለበት ህንፃ 3ተኛ ፎቅ ላይ እንገኛለን፡፡

ስልክ 0902 44 44 41

ጎህ ቤቶች ባንክ አ/ማ በምስረታ ላይ!!